Free tender detail

አዲስ ዘመን ቅዳሜ መጋቢት 25 ቀን 2013 .      

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር NCB/ OEB/GOV/ 23/2013

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ 100 (መቶ) ላፕቶፖችን (Lap-Top) በግልጽ ጨረታ ከአቅራቢ ድርጅቶች በዋጋ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ብቃት ያላቸው ድርጅቶች:

  1. በመስኩ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸው
  2. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመ ጋቢዎች ስለመሆናቸው ማስረጃ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) Number) ያላቸው መሆኑን
  3. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸው ደብዳቤ (clearance) አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀናት ድረስ ዘወትር በመንግስት የሥራ ሰዓት ከሳር ቤት ወረድ ብሎ በሚገኘው የኦሮሚያ ትምሀርት ቢሮ 1 ፎቅ ፋይናንስ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የዕቃውን ቴክንካል እስፔስፈኬሽንና የሚሸጡበትን ዋጋ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ አድራሻቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውን የጨረታ ቁጥሩን እና የአጫራቹን /ቤት ስም በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ ያሉትን ቀናት በመቁጠር (የዕረፈት ቀናትን ጨምሮ) እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከቀኑ 800 ሰዓት ድረስ በሚገኘው የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 1 ፎቅ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በመጨረሻው ቀን በተራ ቁጥር 5 በተገለፀው መሠረት ከቀኑ 8 00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከቀኑ 8 30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ይህ ዕለት የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግሥት የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8.   የጨረታ ማስከበሪያ በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ስም የተዘጋጀ 50,000.00 ( ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ የሚያቀርቡ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ተከፍቶ 45 (አርባ አምስት) ቀናት ይሆናል፡፡ አሸናፊው እንደታወቀ ለተሸናፊዎች ያስያዙት CPO ቆይታውን ሲጨርስ ይመለስላቸዋል፡፡

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ




___________________________________________________________________________________
Category : Computer and Accessories, Computer Purchase, Purchase.
Posted Date : 2021-04-05 02:36:47
Deadline :
2021-04-18 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com