Free tender detail

ሪፖርተር እሁድ መጋቢት 19 ቀን 2013 .      

የጨረታ ማስታወቂያ

ብርሃን ኢንሹራንስ . የካሣ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን

  • ከባድ እና ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎችን፣
  • ሩሎ ማሽን፣
  • የተለያዩ የተሽከረካሪ መለዋወጫዎች፣
  • ኩባንያው ሲገለገልበት የነበረውን የመስክ እና አውቶሞቢል ተሸከርካሪዎችን ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር መሰረት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ከዋናው መስሪያ ቤት መግዛት ይችላሉ::
  2. ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በብርሃን ኢንሹራንስ . የተጎዱ ንብረቶች ማከማቻ ቦታ አቃቂ ቃሊቲ /ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ቃሊቲ 40/60 ኮንደሚኒየም በኩል ገባ ብሎ በተለምዶ የቆላ ዝንብ አካባቢ (ጨፌ ሰፈር) የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ በንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ::
  3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ለመጫረት የሚፈልገውን የንብረት ዓይነት እና ያቀረበውን የጨረታ ዋጋ ዝርዝር በመግለፅ ፤የጨረታ ማስከበሪያ የንብረቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 15 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ . . . በብርሃን ኢንሹራንስ .. ስም በማስያዝ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 6 ቀን 2013 .. ድረስ በሥራ ቀናት ብርሃን ኢንሹራንስ .. ዋናው /ቤት ቂርቆስ /ከተማ ቀበሌ 05/06 የሺታም ህንፃ 4 ፎቅ (ግሎባል ሆቴል አካባቢ ኖክ ነዳጅ ማደያ አጠገብ) በአካል በመገኘት የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ፓስታ ለሚጫረቱበት የዕቃ አይነት ማስገባት ይችላሉ::
  4. በጨረታ ለተሸነፉ ያስያዙት ... ይመለስላቸዋል:: ለጨረታ አሸናፊዎች ደግሞ ያዝያዙት ገንዘብ ለሚገዙት ዕቃ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ይታሰብላቸዋል::
  5.  አሸናፊዎች በጨረታው ላሸነፉት ንብረት ቀሪውን ክፍያ እና 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ አክለው በመክፍል የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ እቃዎችን መረከብ ይኖርባቸዋል:: በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ያሸነፉትን ንብረት ከፍለው ካልወሰዱ ኩባንያው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልጽ ሁኔታ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ካልተገለፀ በስተቀር በቀረበው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል ::
  7. ተሽከርካሪዎች በጨረታ እስከተሽጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ወይም ሌላ ክፍያ የሻጩ ኃላፊነት ይሆናል::
  8. አሸናፊ ተጫራቾች የገዙትን ዕቃ ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጪ አስነስተው ይወስዳሉ::
  9. ጨረታው ሚያዚያ 06 ቀን 2013 . . ከቀኑ 8 00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8 30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር በተያየዘ መገኘት አይጠበቅባቸውም::
  10. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-67-44-23/46 ወይም 0114-70-40-54 በመደወል ይቻላል::


በየቀኑ ጨረታዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ

https://t.me/habeshatender




___________________________________________________________________________________
Category : Machinery., Machinery Sale, Machinery Spare Parts, Sale., Vehicle and Spare Parts, Vehicle Sale, Spare Parts Sale and Supply
Posted Date : 2021-03-30 03:49:24
Deadline :
2021-04-14 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com