Free tender detail

አዲስ ዘመን ማክሰኞ መጋቢት 7 ቀን 2013 .      

ያገለገሉ መኪናዎች የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያፖስታ አገልግሎት ድርጅት የተለያየ ሞዴል ያላቸው ያገለገሉ 24 መኪናዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረትቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) ድርጅቱ ገንዘብ ቤት በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በግዥና አቅርቦት ዲፓርትመንት ቢሮ ቁጥር GO6 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2.  መኪናዎችን ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በዋናው /ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት መኪናዎቹ ያሉበትን ሁኔታ መመልከት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በሰም (በተደፈነ) ኤንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር Go6 ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓም ከቀኑ 6 00 ሰዓት ድረስ ሠነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ መኪናዎቹን ለመግዛት ባቀረቡት ዋጋ ሰረት 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ CPO ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ጋር በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መጋቢት 29 ቀን 2013 . ከቀኑ 8 30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር Go6 ይከፈታል፡፡
  6. በተሸጡ መኪናዎች ላይ የሚፈልግ ቀረጥ ታክስና ውዝፍ ዕዳ ሲኖር መኪናውን እስካነሱበት ቀን ድረስ መሥሪያ ቤታችን ይከፍላል፡፡ ከባለቤትነት ስም ዝውውር ጋር የተያያዙ ወጪዎችን ይሸፍናል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉባቸውን መኪናዎች ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ 10 ቀናት የሚፈለግባቸውን ክፍያ አጠናቀው መኪናዎቹን መረከብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን ክፍያ አጠናቀው ያሸነፉባቸውን መኪናዎችን ለማያነሱ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ለመሥሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
  8. እያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል የሚሸጥ ይሆናል፡፡
  9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

የበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-515 32 72 0115510924

ኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት




___________________________________________________________________________________
Category : Sale., Vehicle and Spare Parts, Vehicle Sale
Posted Date : 2021-03-17 07:03:24
Deadline :
2021-04-07 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com