Free tender detail

አዲስ ዘመን ቅዳሜ መጋቢት 4 ቀን 2013 .      

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 005DC /2013

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግንባታ ሥራዎች የሚሠሩ የተለያየ ደረጃ ያላቸውን ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

  በዚህ መሠረት፤

ተጫራቾችለሥራው ሕጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣ የምዝገባ ምሥክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምሥክር ወረቀት ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ወቅታዊ ታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ አጭር ምዝገባ ያደረጉና 2013 . ያሣደሱ ተጫራቾች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ሎት 1 አቃቂ ቃሊቲ B+G+2 የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ (CAE-1)
  2. ሎት 2 የካ B+G+2 የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ (CAE-1)
  3. ሎት 3 ቦሌ B+G+2 የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ (CAE-1)

1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8 ፎቅ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 የካላንደር ቀናት ድረስ የማይመለስ 200.00 ( ሁለት መቶ ብር ብቻ ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8 ፎቅ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 የካላንደር ቀናት ድረስ የማይመለስ 500.00 ( አምስት መቶ ብር ብቻ ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ በመሙላትና በሰም በማሸግ የጨረታ መመሪያ በሚያዘው መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8 ፎቅ በሚገኘው ሣጥን ውስጥ ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት 22 ኛው የካላንደር ቀን ድረስ ባለው ጊዜ እስከ 4 00 ድረስ የጨረታ ሠነዱን (Technical & Financial Proposal) ለእያንዳንዱ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

3. የቅድመ ብቃት ጨረታ ሠነድ (Technical Proposal ) በዚሁ ዕለት 4 00 ሰዓት ተዘግቶ 4 30 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 801 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሠነዱ ላይ በተቀመጠው መሠረት በባንክ ክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደር አይችልም፡፡ ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሣሰቢያ፡ - የጨረታ መክፈቻው 22 ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ

 




___________________________________________________________________________________
Category : Construction and Construction Machinery, House and Building Construction
Posted Date : 2021-03-15 07:12:29
Deadline :
2021-04-03 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com