Free tender detail

 

አዲስ ዘመን ቅዳሜ ጥቅምት 7 ቀን 2013 .      

የጨረታ ማስታወቂያ

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር PPPDSNP- 14FBL/01/02/2013

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ንብረትነታቸው የቤተመንግስት አስተዳደር፣የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርት ባለስልጣን፣ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ የአካባቢና የደን ምርምር ኢንስቲትዩት፣ የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ፣ የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት፣ የወንዶ ገነት የደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣ የአለርት ሆስፒታል እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ያገለገሉ 30 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመሰከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በገንዘብ ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር 001 በመምጣት የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 300 እስከ 1000 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተጠቀሱት /ቤቶች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
  4. ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ ካለው ባለንብረቱ መሥሪያ ቤት የሚሽፍን ሲሆን የስም ማዛወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው ይሸፈናል፣
  5. ተጫራቾች የሚገዙትን ተሽከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ ነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተ ረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል፡፡ የተሽከርካሪውን የመነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
  6.  የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ምሮ 20 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4 15 ሰዓት ተጫ ራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
  7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው 7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መከፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል::
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን ተሽከርካሪዎች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
  9. አገልግሎቱ ያወጣውን ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሽነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሽከርካሪውን 10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው
  11. ተጨማ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-154-04-25 ወይም 011-122-37-08/36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
  12. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አዲስ አበባ




___________________________________________________________________________________
Category : Sale., Vehicle and Spare Parts, Vehicle Sale
Posted Date : 2020-10-19 05:18:14
Deadline :
2020-11-05 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com