Free tender detail

 

አዲስ ዘመን አርብ መስከረም 29 ቀን 2013 .      

3 ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ብግጨ 16/2013

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 2013 በጀት ዓመት የጎዳና ተዳዳሪ ማገገሚያ ማዕከል ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ስራውን ለመስራት የሚፈልጉ ተጫራቾች

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ለሥራ የሚያስፈልገውን የሰው ኃይል፣ ማቴሪያልና ማሽነሪዎችን ሙሉ በሙሉ በራሱ አቅርቦ መሥራት የሚችል BC6 እና GC-7 እና በላይ የግንባታ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00/ አንድ መቶ ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሠርተው ማቅረብ ሲኖርባቸው በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት /ቤት የዋስትና ደብዳቤ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም በማሠራት ማቅረብ አለባቸው፣
  4. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀለት 7/ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ 8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፣
  5.  ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሥራ ተቋራጮች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ / ብር በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣
  6. ተወዳዳሪ ተቋራጮች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ 22ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 359 ድረስ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
  7. ጨረታው 22 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4 30 ሰዓት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታን ጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይከፈታል።
  8. የጨረታውን ፋይናንሽያል ኦርጅናል ዶክመንቶች እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ሲኖርባቸው ፋይናንሽያል ዶክመንቶች ከኦርጅናሉ በተጨማሪ ኣንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  9. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሣሰቢያ፡ - የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058771-66-91 ደብረ ማርቆስ መጠየቅ ይችላሉ።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ




___________________________________________________________________________________
Category : Construction and Construction Machinery, House and Building Construction
Posted Date : 2020-10-10 02:05:26
Deadline :
2020-10-30 (Bid Closed.)

 
   

Copyright © 2011 - 2024 Habesha Tender
Telephone: +251-118-961881/ +251-911-891169 / +251-920-105191, P.O.Box: 122841
Office Address: Aberus Complex 4th floor, office No 405, Bole Road infront of Dembel City Center
Email: contact@habeshatender.com || Website: www.habeshatender.com